ሸክሸኮ ዋሻና ፏፏቴ (sheki skeko waterfall& cave)

Undefined
timage: 
tbody: 

የሸክሸኮ ዋሻና ፏፏቴ በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ በወሎ እና በቄጃ ቀበሌ መካከል የሚገኝ ሲሆን ከዞኑ ዋና ከተማ ቴፒ በ 100 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ከማሻ ከተማ ወደ ጎሬ  የሚወስደዉን መንገድ ተከትለን 12 ኪ.ሜ የመኪና መንገድ  ከተጓዝን በኃላ ቄጃ ቀበሌ እንደደረስን በደን የተከበበዉን ታርካዊዉንና ተፈጥሮአዊዉን የሸክሸኮ ዋሻና ፏፏቴ እናገኛለን፡፡ሸክሸኮ የሚባል መጠሪያ  ለፏፏቴዉ የተሰጠዉ በሸክኛ አጠራር  ሸክሸኮ ተብለው ከሚጠሩ ከወፍ ዝረያ  ስሆን ወፎችም ከጥንት ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እዚያ ዉስጥ መኖራቸው አግራሞትን የሚጭር ነዉ፡፡ በተጨማሪም ለ bird watch ጎብኝዎችም እርካታን ይሰጣል፡፡ይህ ዋሻና ፏፏቴን ከሌሎች ለየት የሚያደርገዉ ዋሻዉ የዱር አራዊቶች ማደሪያ መሆኑና  ከላይ አይንን የምማርክ ፏፏቴ ከስር በግንበኞች ዲዛይን ተደርጎ የተገነባ አዳራሽ መሳይ ዋሻ ያለዉ ሲሆን እስከ 5000 ሰዉ እንደምይዝ ይገመታል፡፡ ዋሻዉ ጥንት ኢትዮ- ጣልያን ጦርነት ወቅት የአካባቢዉ ሕ/ሰብ  ቤተሰቦቻቸዉንና የቤት እንስሳቶችን  በዋሻዉ ዉሥጥ ደብቀውና  ዋሻዉን እንደ ምሽግ ተጠቅሞ  የጣሊያንን ሠራዊት ድል ያደረጉበት ታርካዊ ዋሻ እንደሆነ  የአካባቢዉ ታርክ አዋቅዎች ይናገራሉ፡፡