በደቡብ ምዕራብ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ዞኖች አጠቃላይ ገጽታ

የዳውሮ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት አስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ ከሚገኙት 6 ዞኖች ውስጥ አንዱ ሲሆን የዞኑ ዋና ከተማ ታርጫ ከአዲስ አበባ በሻሸመኔ ወላይታ ሶዶ 455 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ በጅማ 479 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ዳውሮ ማለት ቃሉ ኩሩ፣ ጀግና የማይበገር ህዝብ ማለት እንደሆኔ መረጃዎች የሚገልጹ ስሆን የቃሉ መጠሪያ አከባቢውንና ብሔረሰቡን ይውክላል። የብሔረሰቡ ቋንቋ ዳውሮኛ የሚባል ስሆን እስከ ኮለጅ ራሱን የቻለ ድፓርትመንት እና በዩንቭረስቲ እንደኮርስ በመሆን እየተሰጠ ይገኛል። የዞኑ ጂኦግራፊያዊ መገኛ በ60.59-70.3 ሰሜን «ላቲትዩድ» እና በ360.6-370 3 ምስራቅ... Read More
የኮንታ ዞን በደ/ም/ህ/ክ/መ/ ከሚገኙት ዞኖዎች መካከል አንዱ ሲሆን የዞኑ ዋና ከተማ አመያ ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ከቦንጋ በ215 ኪ .ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ርዕሰ ከተማው በአዲስ አበባ በጅማ በኩል 454 ኪ.ሜ ሲሆን ዞኑዉ በሰሜን ከኦሮሚያ፣ በደቡብ ከደቡብ ኦሞ ዞን፣ በምስራቅ ከዳዉሮ ዞን፣ በምዕራብ ከከፋ ዞን፣ በደቡብ ምስራቅ ከጋሞጎፋ ዞን ጋር ይዋሰናል፡፡ የዞኑ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 2554.2 ካሬ ኪ.ሜ ሲሆን የህዝብ ጥግግት በካሬ ኪሎ ሜትር 41 እንደሆነ ከክልሉ ስነ-ህዝብና ስታስትክስ የተገኘ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡በዞኑ በሚገኙ 8የከተማና 44 ገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ከ300 ሺ በላይ ህዝብ ይኖራል... Read More
የዞኑ አስትሮኖሚያዊና አንጻራዊ መገኛ የሸካ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ከሚገኙ 5 ዞኖች አንዱ ሲሆን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በላቲትዩድ መስመር 7.12-7.89 ዲግሪ ሰሜን ሎንግቲዩድ መስመር 35.24-37.90 ዲግሪ ምስራቅ የሚገኝ ሲሆን አዋሳኞቹም በሰሜን ከኦሮሚያ ክልል ኢሉአባቦራ ዞን በደቡብ ከቤንች ማጂ ዞን በምስራቅ ከካፉ ዞን በምዕራብ በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን ናቸው፡፡ የዞኑ ቆዳ ስፋት የዞኑ ቆዳ ስፋት 238750 ሄ/ር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 61.7% በደን የተሸፈነ ሲሆን የዚህም ዋነኛ ምክንያት የህሰቡ ጠንካራ የደን ጥበቃ ባህል ለረዥም ጊዜ ጠብቆ ያቆየው ነው፡፡ ከሌሎች... Read More
ምዕራብ ኦሞ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከሚገኙት ዞኖች መካከል አንዱ በመሆን በሚያዝያ 23/2011 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን ውብ የመሬት አቀማመጥና ማራኪ የተፈጥሮ ሀብት ያለው ፣ ቡና መገኛ ከሆነው ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከሚገኙ ዞኖች አንዱ ነው፡፡ በሀገርቱ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ 671 ኪ/ሜትር ከቦንጋ 197 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል ፡፡ ዞኑ በሴሜን ምዕራብ ቤንች ሸኮ ዞን፤በደቡብ ምስራቅ ከደቡብ ኦሞ ዞን ፤ በደቡብ ምዕራብ ከጋምቤላ ክልል መዣንግ ዞንና፤ከደቡብ በደቡብ ሱዳን ሪፓብሊክ ጋር ይዋስናል፡፡ ዞኑ በሰባት ወረዳዎች በ115 ቀበሌና በሶስት ከተማ አስተዳደር የተከፋፈለ ሲሆን የቆዳ... Read More