ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ የሚያኮሩ አትሌቶችን ለማፍራት እንሰራለን~የሁለተኛ ደረጃ አትሌቲክስ አሰልጣኞች

ssimage: 
Undefined
ssbody: 

ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ የሚያኮሩ አትሌቶችን ለማፍራት እንሰራለን~የሁለተኛ ደረጃ አትሌቲክስ አሰልጣኞች
በአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ፕሮጀክቶች ላይ በንቃት በመሳተፍ ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ የሚያኮሩ አትሌቶችን ለማፍራት እንደሚሰሩ የሁለተኛ ደረጃ አትሌቲክስ አሰልጣኞች ገለጹ፡፡
በየአካባቢያቸው በሚገኙ የአዳጊዎች አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ፕሮጀክቶች በሙያቸው በማገልገል ኢትዮጲያ በአትሌቲክሱ ያላትን ታሪክ ለማሰቀጠል ተግተው እንደሚሰሩ ተናግረዋለ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ሰፖርት ቢሮ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን ጋር በመተባበር ለ15 ቀናት በቦንጋ ከተማ ሲሰጥ የቆየው የአትሌቲክስ አሰልጣኝነት ስልጠና ተጠናቋል፡፡
በስልጠናው ከ6ቱም ዞኖች የተውጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ ከሰልጣኞች መካከል አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት ሀገር-አቀፍ እና ዓለም-አቀፍ እውቅና ባላቸው ኢንስትራክተሮች በተግባርና ንድፈ-ሀሳብ በቂ እውቀት ማግኘታቸውን ገልጠዋል፡፡
ምንም እንኳ ለዘርፉ ውጤታማነት የቁሳቁሰ ዕጥረት ስጋት ቢሆንም ያሏቸውን ቁሳቁሶች ከልምዳቸው ጋር በማቀናጀት በየአካባቢያቸው ያሉ አዳጊ አትሌቶችን በማፍራት ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ መድረክ ያላትን ታሪክ ለማስቀጠል ተግተው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል::
በማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ሀላፊና የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ ኢንጅነር አህመዲን አወል እንደገለጹት፤ ላለፉት ዓመታት ምንም ዐይነት እንቅሰቃሴ ላይ ያልነበረውን የክልሉን አትሌቲክስ ለማነቃቃት በተደረገው ድጋፍ የባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱ መነሳሳትን የፈጠረ ነው፡፡
አሰልጣኞች ያገኙትን እውቀት እና ክህሎት ከነበራቸው ልምድ ጋር በማቀናጀት የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ተስፋ ማድረጋቸውን የተናገሩት ኢንጅነር አህመዲን፤ መሰል ስልጠናዎች በሌሎች የስፖርት ዓይነቶችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
አስልጣኞች አዳጊ ወጣቶች ላይ በትኩረት በመስራት ለአትሌቲክስ ሰፖርት ዕድገት አበርክቷቸውን እንዲያኖሩ ጥሪ አቅርበዋል፡:
የክልሉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘካሪያስ ሀይሌ በበኩላቸው፤ 31 ሰልጣኞች የተዘጋጀላቸውን የተግባርና የጽሁፍ ፈተና ከ70 በላይ የሆነ ውጤት በማምጣት ማለፍ ችለዋል ብለዋል፡፡
ከነዚህም ውስጥ ሰባቱ አሰልጣኞች ሴቶች ስለ መሆናቸው ገልጸዋል።
ለአሰልጣኞች የአሰልጣኝነት ሰርትፍኬት፣ ለስራው ስኬታማነት አሰተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና ድርጅቶች እንዲሁም ለሌሎች ባለድርሻ አካላት የዕውቅናና የምስጋና ሸልማት ተበርክቷል፡፡