የሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ ግንባታ ከፊል ርክብክብ ተደረገ።

ssimage: 
Undefined
ssbody: 

የሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ ግንባታ ከፊል ርክብክብ ተደረገ።

ግንቦት 17/2015ዓ.ም

ሚዛን አማን

የሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ ግንባታ ከፊል ርክብክብ በዛሬዉ ቀን ተፈጽሟል።

የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ የስፖርት አካዳሚዉ በቀጣይ በጀት ዓመት ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማሰልጠን እንድጀምር አሁን ባለበት ደረጃ ከፊል ርክብክብ መደረጉን ገልፀዋል።

የሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚን ወደሥራ ለማስገባት ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ስሰሩ መቆዬታቸዉን የጠቆሙት የቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ የቀሪ አጥር ግንባታ; የሜዳ ዙሪያ ሥራ እና የዉሃና የመብራት አገልግሎት የቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቶ በአጭር ጊዜ ዉል በማጠናቀቅ አካዳሚዉ ለሰልጣኞች ክፍት እንዲሆን ይሰራል ስሉ ገልፀዋል።

የክልሉ ማህበረዊ ዘርፊ ልዩ አማካሪ አቶ ደነቀ ማሞ በበኩላቸዉ ክልሉ በርካታ ስፖርተኞችን ማፍራት የሚችል አቅም እንዳለዉ ጠቁመዉ የተጎደለዉ እና መሰረታዊ ነገሮች በአጭር ጊዜ ተሟልተዉ አካዳሚዉ ወደሥራ የሚገባበትን ሁኔታ እንደሚያመቻቹ ገልፀዋል።

የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ም/ል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አህመዲን አወል አካዳሚዉ በቀጣይ ዓመት ሥራ የሚጀምረዉ በአትሌትክስ ቨዘርፍ ብቻ መሆኑን ጠቅሰዉ ቀጣይ በስምንት ስፖርት ዘርፍ ከሁለት መቶ በላይ ሰልጣኞችን ተቀብሎ እንደሚያሰለጥን ጠቁመዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ በበኩላቸዉ

ግንባታዉ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ደርሶ ለሶስት ዓመታት ያለ ሥራ መቆዬቱ ተገቢ ያለመሆኑን በመጥቀስ የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ከፊል ርክብክብ አስፈጽሞ አካዳሚዉን በቀጣይ በጀት ዓመት ወደተግባር እንዲገባ በሚያደርገዉ ሂደት የዞኑ መንግስት ተገቢዉን ሁሉ እንደሚደግፍ ገልፀዋል።

የክልሉ ኮንስትራክሽን ባለሙያ እንጅነር ዮሐንስ ጎበዜ በ2010ዓ.ም ግንባታዉ የተጀመረዉ ይህ የስፖርት አካዳሚ 53 ሚሊዮን ብር ብቻ ነፈጀ መሆኑን በመጠቆም በአሁን ጊዜ የፊዝካል አፈጻጸም 87%; የፋይናንሻል አፈጻጸም 83% እንደሆነ ገልፀዉ መሰረታዊ የሆኑ የመብራትና የዉሃ አገልግሎት በአፋጣኝ ቢሟላ ህንጻዉ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማስተናገድ እንደሚችል አብራርተዋል።

ዘገባዉ የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ነዉ።