የምዕራብ ኦሞ ዞን አጠቃላይ ገፅታ

zoneb: 

ምዕራብ ኦሞ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከሚገኙት ዞኖች መካከል አንዱ በመሆን በሚያዝያ 23/2011 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን ውብ የመሬት አቀማመጥና ማራኪ የተፈጥሮ ሀብት ያለው ፣ ቡና መገኛ ከሆነው ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከሚገኙ ዞኖች አንዱ ነው፡፡ በሀገርቱ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ 671 ኪ/ሜትር ከቦንጋ 197 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል ፡፡ ዞኑ በሴሜን ምዕራብ ቤንች ሸኮ ዞን፤በደቡብ ምስራቅ ከደቡብ ኦሞ ዞን ፤ በደቡብ ምዕራብ ከጋምቤላ ክልል መዣንግ ዞንና፤ከደቡብ በደቡብ ሱዳን ሪፓብሊክ ጋር ይዋስናል፡፡
ዞኑ በሰባት ወረዳዎች በ115 ቀበሌና በሶስት ከተማ አስተዳደር የተከፋፈለ ሲሆን የቆዳ ሲፋት 14,548 ስኩዌር ካሬ ኪ/ሜትር እንደሚሆንና በስኩዌር ካሬ ኪ/ሜትር በአማካኝ 59 ህዝብ እንደምኖር ይገመታል ፡፡
የ1999 ዓ.ም የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት መሰረት በማድረግ በተደረገው ትንቢያ በ2013 ዓ.ም የዞኑ የህዝብ ብዛት ወ 144,174 ሴ 147,635 ድምር 291,809 በዞኑ ማዕከልና በ7ቱ ወረዳዎች የሚገኙ አራቱ/4/ ነባሪ ብሄረሰቦች ማለትም የመኤንት፤የዲዝ ፤የሱርማ፤የዝልማሞ ብሄረሰቦችንና በሰፈራ ተካቶ ያሉ የአማራ፤የሲዳማና የከንባታ ብሄረሰቦችን ያካተተና በተጨማሪም በዞኑ ውስጥ ባሉ ወረዳ ከተማዎች በንግድና በመንግስት ስራ የተሰማሩ ሌሎች ኢትዮጵያዊ ብሄረሰቦች ይኖራሉ፡፡
በዚህ ዞን ውስጥ በዋናነት ካሉት ነባር ብሔረሰቦች የመንኤት፤የዲዚ፤የሱርማና የዝሊማሞ ብሔረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን ከነባር ሕዝብ ጋር በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በአንድነት ተሰባስበዉና ተፈቃቅረው ተከባብረው የሚኖሩበት አካባቢ ነው፡፡ አብዛኛው ህዝብ የሚተዳደረው በከፊል አርብቶ አደርነት፤በግብር እና በማዕድን ምርት የሚተዳደር ህዝብ ጨምሮ የያዘ ነው፡፡የህዝብ አሰፋፈሩ በመኖርያ አካባቢ በገጠር 208,906(71.59%) እና በከተማ 82,903 (28.41) ህዝብ እንደሚኖር ይገመታል ፡፡
በዞኑ መልከዓ ምድራዊ አቀማመጥ ከባህር ጠለል በላይ ከ500-3000 ሜትር ወሰን ዉስጥ የሚገኝ በመሆኑ የአየር ፀባዩ ለተለያዩ የግብርና ስራዎች ምቹ ነው፡፡ አመታዊ የዝናብ አማካይ መጠን ከ400-2000ሚ/ሜ ነው፡፡ አማካይ የሙቀት መጠን 15.1c-27.5c ይደርሳል፡፡ ከስነ ምህዳር ስብጥር ቆላማ 52% ፤ወይናደጋ 43% እና ቀርው 5% ደጋ የአየር ፀባይ አለው ፡፡ ዞኑ በተለይ የሀገርቱ የውጭ ምንዛሪ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የቡና ፤የቅመማቅመም ፤ሩዝና ሰሊጥ ምርት ፤የተለያዩ የዕምቅ ሀብት ባለቤት ሲሆን ለአብነተ ሊጠቀሱ የሚችሉ የኮንስትራሽን ማዕድናት፤ወርቅ፤ዕምነበረድ ሌሎች የተለያዩ የከበሩ ማዕድናት ፤ ሚሽን ዋሻ፤እግዝሔር ድልድይ ፤የገጸ ምድር ዉሃ፤ ሻሁማች ዋሻ፤ከዩና ዋሻ፤ጎጉቱ ባሽክሰ ዋሻ፤ኤልጎዳም ዋሻ፤ጋቦና ዋሻ፤ከረች ደን፤ኩይ ፍል ውሃ፤ጋይድ ፍል ውሃ ፤ዱሉም ፍል ውሃ በሻሻ ወረዳ የጎሪ ጌሻ ቡና፤ባለቃ ዋሻ፤ጋይቡ ዋሻ፤ፍል ውሃ፤የቶላ ተክል ድንጋይ ፤ጎሪ የተፈጥሮ ደን፤ካራማች የተፈጥሮ ደን፤ማቶላ ፏፏቴ በጎሪ ጌሻ ወረዳ ሳት ዋሻ፤ጎማ ዋሻ፤ባኒ ዋሻ፤ባድሊ ዋሻና ፏፏቴ፤ያርጣ ፍል ውሃ በመ/ጎልዲያ ወረዳ ኮቡት ዋሻ፤ፋይዳች ዋሻ፤ሀሙት የተፈጥሮ ደን ዋሻናፀበል ይጥ ፏፏቴ፤ተራማጅ ዋሻና ፏፏቴ፤ዶል ፏፏቴ፤ዲሩ ዋሻ፤ጋንቱ ዋሻ፤በርበር ዋሻ፤ተራማጅ ደን በጋቺት ወረዳ ንፋስ በር፤ውርግ ጥቅጥቅ ደን፤አኩ ፏፏቴ፤የጣሊያን ጡብ ቤቶች፤ኮልቡ ደን፤ባንጋ ደን፤ሀሮ ዋሻ፤ሳይ ዋሻ፤እልል ባይ ፍል ውሃ፤ቱም ፏፏቴ፤ኮምቲ ኬያዝ ፋፋቴ፤ቱፋ ፏፏቴ በማጅ ወረዳ የሱርማ ብሔረሰብ ባህል፤ጎጎርም ዋሻ፤የበርየም ፏፏቴ፤የባሉናኑ ዋ፤ጎያ ፍል ውሃ በሱርማ ወረዳ የወጣቶች ትግል ሜዳ፤የባለ ሀብቶች መቃብር፤ደንብ መሰሪያ ቦታ፤የደርግ ወታደር ምሽግ፤ፀበል ቦታ፤ጃባ ብርጅ ተራራ፤የኩርፋ ዋሻ፤ፃና ፋፈቴ በቤሮ ወረዳ ሲሆን ዞናችን የተያዩ ዓይነት ያላቸው እፅዋትና እንስሳት የሚኙበት ዞን ሲሆን በክልሉ ከሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮች ዉስጥ አንዱ የኦሞ ብሔራዊ ፓርክ በዚህ ዞን ይገኛል፡፡