የክለቦች ሻምፕዮና ዉድድር ግንቦት 19 | 2015 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገለፀ !!

ssimage: 
Undefined
ssbody: 

የክለቦች ሻምፕዮና ዉድድር ግንቦት 19 | 2015 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገለፀ !!

ግንቦት 15 | 2015 ዓ.ም

ታርጫ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የክለቦች ሻምፕዮና ዉድድር ግንቦት 19/2015 ዓ.ም በቦንጋ ከተማ እንደሚጀመር የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ ገልፀዋል።

የክልሉ የእግር ኳስ ፌደሬሽን ከስፖርት ባለሙያዎች ጋር በመሆን ዉድድሩ የሚካሄድበት ዞን የዝግጅት ምዕራፍን በተመረጡ ሶስት ዞኖች ማለትም በሸካ፣ በካፋ፣ እና በዳዉሮ ዞን ተዘዋውረው ገምግመዉ ባቀረቡት መነሻ በካፋ ዞን በቦንጋ ከተማ እንዲካሄድ መወሰኑን ኃላፊዉ ገልፀዋል።

በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደዉን የክለቦች ሻምፕዮና ዉድድር በሚመለከት የእግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢብራሂም ተማምን ጨምሮ የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች በዛሬዉ ቀን ዉይይት አድርገዋል።

የክልሉ የእግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንትና የጤና ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ተማምም ከግንቦት 19/2015ዓ.ም ጀምሮ በቦንጋ ከተማ የሚካሄደዉ የክለቦች ሻምፕዮና ዉድድር ተወዳዳሪዎች ችሎታቸዉን የሚያሳዩበትና ለአገር አቀፍ ዉድድር የሚመለመሉበት ዕድል እንደሚፈጥር ጠቅሰዉ ዉድድሩ ፍፁም ሰላማዊና ስፖርታዊ ጨዋነት የተሞላበት እንዲሆን አሳስበዋል።

ትልልቅ የአዉሮፓ ክለቦች ተጫዋቾች ከአፍሪካ ትንንሽ መንደሮች የተወጣጡ መሆናቸዉን የጠቆሙት የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ም/ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አህመዲን አወል ክልሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉን የእግር ኳስ ተጫዋቾችን ማፍራት እንደሚችል ጠቁመዉ ከዚህ ዉድድር ብቃት ያላቸዉ ተጫዋቾች ለሃገር አቀፉ ዉድድር ተመልምለዉ ክልሉን እንደሚወክሉ ገልፀዋል።