የክልሉ ምክር ቤት አባላትና ከፍተኛ አመራሮች በዳውሮ ዞን የለማ የበልግ በቆሎ ማሳ ጎበኙ።

የክልሉ ምክር ቤት አባላትና ከፍተኛ አመራሮች በዳውሮ ዞን የለማ የበልግ በቆሎ ማሳ ጎበኙ።
የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ እየተሳተፉ የሚገኙ የምክር ቤት አባላት በጉብኝቱ ተሳታፊ ነበሩ።
በጉብኝቱም በአርሶአደር ገዛኸኝ ገቲሣ 6.5 ሄክታር በሆነ መሬት የለማውን የካዛባ ምርት የጉብኝቱ አካል ነው።
ዞኑ በበልግ እርሻ ወቀት ከ37 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳን በዘር መሸፈኑን የገለጹት የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታመነ ከዚህም ውስጥ 20ሺህ ሄክታር ማሳ በቦቆሎ ምርት መሸፈኑን ተናግረዋል።
በወረዳው ዋራ ክላስተር በኩታ ገጠም የበልግ እርሻ 714 ሄክታር መሬት መልማቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታመነ ተስፋዬ አስረድተዋል።
በጉብኝቱም የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የበቆሎ ምርት ከቤት ፍጆታ በተጨማሪ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀመታ ያለው በመሆኑ የተሻለ ምርት ለመሰብሰብ የእርሻ ተክኖሎጂ በመጠቀም በቀጣይ የምርት ዘመን ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
በጉብኝቱም የክልሉ ዋና አፈጉባኤ ክቡር አቶ ወንድሙ ኩርታ ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ የክልሉ ምክርቤት አባላትና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።

Undefined
Image: