የኮንታ ዞን አጠቃላይ ገጽታ

zoneb: 

የኮንታ ዞን በደ/ም/ህ/ክ/መ/ ከሚገኙት ዞኖዎች መካከል አንዱ ሲሆን የዞኑ ዋና ከተማ አመያ ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ከቦንጋ በ215 ኪ .ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ርዕሰ ከተማው በአዲስ አበባ በጅማ በኩል 454 ኪ.ሜ ሲሆን ዞኑዉ በሰሜን ከኦሮሚያ፣ በደቡብ ከደቡብ ኦሞ ዞን፣ በምስራቅ ከዳዉሮ ዞን፣ በምዕራብ ከከፋ ዞን፣ በደቡብ ምስራቅ ከጋሞጎፋ ዞን ጋር ይዋሰናል፡፡
የዞኑ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 2554.2 ካሬ ኪ.ሜ ሲሆን የህዝብ ጥግግት በካሬ ኪሎ ሜትር 41 እንደሆነ ከክልሉ ስነ-ህዝብና ስታስትክስ የተገኘ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡በዞኑ በሚገኙ 8የከተማና 44 ገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ከ300 ሺ በላይ ህዝብ ይኖራል፡፡
በኮንታ የፃራ፣የማንጃና የባጫ ጎሳዎች ከነባር ህዝብ ጋር አብሮ የሚኖር ሲሆን በምግብ ዋስትና ፕሮግራም ከሀድያ፣ከወላይታናከአማራ የመጡ አልሚ አርሶ አደሮች ከዞኑ ሕዝብ ጋር በስብጥር ይኖራሉ፡፡
የዞኑመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ሜዳማ፣ተራራማና ተዳፋት ሲሆን ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ ከ870-2850 ሚ.ሜ ነው፡፡በዚህ መሰረት የልዩ ወረዳው አየር ንብረት ክልል በ6% ደጋ በ54% ወይና ደጋና በ40%ቆላማ የአየር ንብረት የተከፋፈለ ነው፡፡
በዞኑያለው የአየር ጸባይ እርጥበት ያዘለ ደጋ፣ወይና ደጋና እርጥብ ቆላማነት ሲኖረው ዓመታዊ የዝናብ ስርጭት 1200-2290 ሚ.ሜ የሚደርስ ነው፡፡የዝናብ ስርጭቱም ከ 8-10 ወር የሚዘልቅ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ በዞን ያለዉ የውኃ ሀብት መጠን ከፍተኛ ሲሆን ዓመቱን ሙሉ የማይደርቁ ወደ 11የሚጠጉ ወንዞችና 5 ሐይቆች ይገኛሉ፡፡
የህዝብ አሰፋፈር በተመለከተ ከዞኑ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት 8%በደጋ 52% በወይና ደጋ እና 40% በቆላ የሚኖሩ ናቸው፡፡የምርት ወቅቶች በበልግና በመኸር ሲሆን ከአየር ንብረቱ ጋር ተስማሚነት ያላቸው ለዕለት ፍጆታና ለገበያ የሚውሉ ምርቶች ይመረታሉ፡፡እነሱም በቆሎ፣ ማሽላ፣ገብስ፣ጠፍ፣ስንዴ፣ባቄላ፣አተር፣ለውዝ፣ሰሊጥ፣ተልባ፣ዝንጂብል፣ኮረርማ፣ጥምዝ፣ቡና፣
ሙዝ፣ማንጎ፣አቡካዶ፣ፓፓዬ የተለያዩ አታክልቶች እና እንሰት በብዛት ይመረታሉ፡፡
እንዲሁም ዞናችን ለእንስሳት እርባታ ምቹና ተሰማሚ የአየር ንብረት ያለው ሲሆን የቀንድ ከብት 166,400፣ በግ 35,764፣ ፍየል 29,282፣ ዶሮ 172,694፣ፈረስ 5,233፣በቅሎ 4,740፣ አህያ 4,740 እና የንብ ቤተሰብ 110,420 እና የዓሣ ዝርያ ዓይነት 12 ናቸው፡፡
በዞንካለው ጠቅላላ የቆዳ ስፋት በቋሚ ሰብል የተሸፈነ 4830 ሄ/ር፣ በዓመታዊ ሰብል የተሸፈነ 30103 ሄ/ር፣ በተፈጥሮ ደን የተሸፈነ 63300ሄ/ር ወደፊት ሊለማ የሚችል 76625 ሄ/ር ሊለማ የማይችል 9789ሄ/ር እና በሌሎች በተለያዩ ነገሮች የተሸፈነ 5664 ሄ/ር ሲሆን የመሬት አቀማመጡም 15% ሜዳ 50% ተዳፋትና 35% ተራራማ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ካለው ሰፊ የተፈጥሮ የደን ሽፋን 63300 ሄ/ር መሬት በጥብቅ የደን ክልል የተከለለ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ወደ ብሔራዊ ፓርክ ደረጃ የተከለለ የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ 125215 ሄ/ር ነው፡፡ፓርኩ በተፈጥሮ አቀማመጥ ወጣ ገባና ሜዳማ ሲሆን ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 700-2600 ሚ.ሜ የሚደርስ ነው፡፡የጨበራ ጩርጩራ ብ/ፓርክ ከአ.አ በጅማ በኩል እስከ ዞኑው ርዕሰ ከተማ አመያ ድረስ 454 ኪ.ሜ ሲሆን የፓርኩ መነሻ ከዞኑው ሁለተኛ ከተማ ጪዳ 5 ኪ.ሜ ገባ ብሎ ከኬርበላ ቀበሌ የሚጀምር በመሆኑ ይህም ከአ.አ አመያ በሚያቋርጠው ጎዳና ላይ ይገኛል፡፡በሌላ በኩል ከዞኑው ዋና ከተማ አመያ 13 ኪ.ሜገባ ብሎ የፓርኩን ዋና መግቢያ መሐል አቋርጦ እስከ 67 ኪ.ሜ የፓርኩ መጨረሻ ድረስ የሚያስኬድ የበጋና የክረምት መንገድ አለው፡፡