የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።
የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ በታርጫ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባዔ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ምክርቤቱ ባለፈው በጀት ዓመት በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል ።
አፈ-ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ ምክር ቤቱ በህገ መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሠረት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሲወጣ መቆየቱንና ለታችኛው መዋቅር ሁሉአቀፍ ድጋፍ ከማድረግ አንጻር በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል ።
በታችኛው መዋቅር የሚታዩ ክፍተቶችን ከስሩ ለመፍታት የምክርቤት አባላት አጽንዖት እንዲሰጡበት ጠይቀዋል።
ምክር ቤቱ በሁለት ቀናት ቆይታ የክልሉ የምክር ቤት ፣የአስፈጻሚ አካላት፣የጠቅላይ ፍ/ቤት እና ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት የ2015 አፈጻጸምና የ2016 ዕቅድ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤የክልሉ መንግስት ከዕቅድ በላይ የተሰበሰበ ገቢ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ማጽደቅ፤የክልሉን መንግስት የ2016 በጀት ዓመት የበጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ማጽደቅ እና የተለያዩ ሹመቶችን መርምሮ ማጽደቅን በአጀንዳነት ይመለከተዋል።

Undefined
Image: