የዳውሮ ዞኑ አጠቃላይ ገጽታ

zoneb: 

የዳውሮ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት አስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ ከሚገኙት 6 ዞኖች ውስጥ አንዱ ሲሆን የዞኑ ዋና ከተማ ታርጫ ከአዲስ አበባ በሻሸመኔ ወላይታ ሶዶ 455 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ በጅማ 479 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ዳውሮ ማለት ቃሉ ኩሩ፣ ጀግና የማይበገር ህዝብ ማለት እንደሆኔ መረጃዎች የሚገልጹ ስሆን የቃሉ መጠሪያ አከባቢውንና ብሔረሰቡን ይውክላል። የብሔረሰቡ ቋንቋ ዳውሮኛ የሚባል ስሆን እስከ ኮለጅ ራሱን የቻለ ድፓርትመንት እና በዩንቭረስቲ እንደኮርስ በመሆን እየተሰጠ ይገኛል።
የዞኑ ጂኦግራፊያዊ መገኛ በ60.59-70.3 ሰሜን «ላቲትዩድ» እና በ360.6-370 3 ምስራቅ ሎንግቲዩድ መስመሮች የሚገኙ ሲሆን በደቡብ የጋሞ ጎፋ ዞን፣ በሰሜን የኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን፣ በሰሜን ምስራቅ የካንባታ ጠንባሮ ዞን፣ በምስራቅ የወላይታ ዞን እና በምዕራብ የኮንታ ዞንን ያወስናል፡፡ ዞኑ ከባህር ወለል በላይ ከ550 እስከ 2820 ሜትር ከፍታ ያላቸውን ሥፍራዎች ይሸፍናል፡፡ የመልካዓ-ምድር አቀማመጡ ወጣገባ፣ ኮረብታማና ተራራማ ሆኖ በሦስት ዋና ዋና የስነ ምህዳር ቀጠናዎች ይካፈላል፡፡ እነዚህም 38 በመቶ ቆላማ፣ 41 በመቶ ወይናደጋና 21 በመቶ በደጋ እንደተሸፈነ ይታመናል፡፡ ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን ከ1374.2 እስከ 2271.6 ሚሊ ሊትርና አመታዊ የሙቀት መጠን ከ15-10c-27.50c ድግሪ ሴንቲ ግሬድ ይደርሳል፡፡
የዞኑን ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ያረጋገጠ አመቺና አሳታፊ የሆነ የፖለቲካ ሥርዓት በመዘርጋት አሳታፊ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ መዋቅር ተዘርግቷል፡፡ በዚሁ መሠረት በዳዉሮ ዞን 10 ወረዳዎችና 2 ከተማ አስተዳደሮች አሉ፡፡ እነዚህም ሎማ፣ ማረቃ፣ ማሪ ማንታ፣ ቶጫ፣ ኢሠራ፣ ከጪ፣ ገና፤ ዛባ-ጋዞ፣ ዲሳ እና ታርጫ ዙሪያ ወረዳዎች ሲሆኑ፤ የታርጫ እና የገሣ ከተማ አስተዳደር ከወረዳ ጋር እኩል መዋቅር ያላቸዉ ናቸዉ፡፡ በዞኑ ባሉ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች በቁጥር 162 የገጠር እና 19 የከተማ ቀበሌዎች እንደሁም፤ 1 ሪፎርም ማዘጋጃ ቤትና 17 ታዳጊ ማዘጋጃ ቤቶች ተደራጅቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛሉ፡፡