የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ አጠቃላይ ገጽታ

Amharic
timage: 
tbody: 

የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ዳውሮና ኮንታ ዞኖች ውስጥ ይገኛል፡፡ የብሕራዊ ፓርኩ አጠቃላይ ስፋት 1410 ኪሎ ሜትር ስኬር ስሆን ከአዲስ አበባ በጅማ 485 ኪ/ሜና ከአዲስ አበባ በወላይታ ሶዶ 510 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

ጨበራ ጩጩራ ብ/ፓርክ በቅርብ ጊዜ ከተቋቋሙትና ህጋዊ ሰውነት ካገኙት ብ/ፓርኮች መካከል አንዱ ነው፡፡ ይህ ብ/ፓርክ በአገራችን ከሚገኙ ብ/ፓርኮች ጋር ሲነጻፀር በብዝሀ ህይወት ሀብቱ የበለጸገና በአንጻራዊነት የተፈጥሮ ይዘቱን ጠብቆ የሚገኝ ነው፡፡ ብ/ፓርኩና በዙሪያው የሚገኙ ስፍራዎች ወሳኝ የሆኑ ሥነ ምህዲራዊ፣ ባህሊዊና፣ የውሀ አካላትን የያዙ ናቸው፡፡ ከብ/ፓርኩ ደጋማ አካባቢዎች መንጭተው ወደ አሞ ወንዝ የሚፈሱ ከ55 በላይ ወንዞችና ጅረቶች ይገኛል፡፡ በብ/ፓርኩና በዙሪያው የሚገኙ የውሀ አካላት እና ተፊሰሶች በአካባቢው እየተከናወኑ የሚገኙና ወደፍት የሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች እንዱሁም በታችኛው ተፊሰስ የሚገኙ የአርብቶ አደር ማህበረሰቦች ከፌተኛ የሆነ የሥነ ምህዳር አገሌግልቶችን የሚሰጡ ናቸው፡፡
እስካሁን በተደረጉ ውስን ጥናቶች በብ/ፓርኩ 40 ትልልቅና መካከለኛ አጥቢ የዱር እንስሳትና ከአውራሪስ በቀር አራቱ ትልልቅ የስፖርታዊ አደን እንስሳቶች (Big Game Animals) ማለትም የአፌሪካ ዝሆን፣ ጎሽ፣ ነብርና አንበሳን በጥሩ ሁኔታና ቁጥር ይገኙበታል፡፡ ለሎች አጥቢ የደር እንሳሳት ለአብነትም የመጥፊት አደጋ የተጋረጠበት ተኩሊ (wild dog)፣ ትሌቁ የደር አሳማ፣ አቦሸማኔ፣ ጉማሬ፣ አዞ እና ላልች 18 ትናንሽ አጥቢ የደር እንስሳት የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አንዱ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ ነው፡፡ በተጨማሪም በብ/ፓርኩ 137 የአዕዋፍ ዝርያዎች በጥናት የተለዩ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ስዴስቱ በአገራችን ብቻ የሚገኙ ብርቅዬዎች ናቸው፡፡ ብ/ፓርኩ ሰፊ ጥናት ቢደረግበት በርካታ የዱር ህይወት ዝርያዎች ልገኙ እንደሚችሉ ይታመናል፡፡ ለአብነትም በ2002 ዓ.ም. በተደረገ ጥናት በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝና ጋራ ጨበራ የተሰኘ አንድ ወርቃማ የዓሳ ዝርያ እንዱሁም በአገራችን በጨበራ ጩርጩራ ብ/ፓርክ ብቻ የሚገኝ ሁለት የሚዲቋ ዝርያዎች ተገኝተውበታል፡፡
የእጽዋት ሽፋኑ በአራት ዋና ዋና ምድቦች የተከፈለ ሲሆን እነዚህም እንጨት ለበስ የሳር መሬት (60%)፣ የተራራ ሊይ ደን (29%)፣ የወንዝ ዳር ደን (3%) እና እንጨት ለበስ መሬት (8%) ናቸው፡፡ በእንጨታማ የዕጽዋት ዝርያ ሊይ በተደረገ ብቸኛ ጥናት 106 እንጨታማ የእጽዋት ዝርያዎች የተገኙ ሲሆን ከእነዚህም መካከሌ ስድስቱ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ናቸው፡፡ ብ/ፓርኩ በአገሪቱ የምድር ወገብ እርጥበታማ ደኖች (Equatorial rainforest) ከሚገኙባቸው ጥቂት አካባቢዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ብ/ፓርኩ ቅመማቅመም፣ ቡና፣ የስራስርና ለመዴኃኒትነት የሚያገለግል ዕጽዋቶች፣ ጌሾ፣ ጫትና የዕጣን ዛፌን የመሳሰሉ የዱር ዝርያዎች (wild varieties) በብዛት የሚገኙበትና ወሳኝ የሆነ የዘረ-መሌ ምንጭ በመሆን የሚያገለግል ነው፡፡
ብ/ፓርኩ በአሁኑ ወቅት በአንጻራዊነት ከሰዎች ንክኪ ነጻ የሆነ ቢሆንም የሰውና የዱር እንስሳት ግጭት ከጊዜ ወደ እየጨመረ በመምጣቱ የአከባቢውን ማህበረሰብ እያስቆጣ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ለችግሩ መፍተሄ በማበጀት ብሄራዊ ፓርኩን ከመጠፋት እንዲታደግ ጥሪውን አናቀርባለን፡፡

መንግስት የጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክን ምቹ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በገባዉ ቃል መሰረት ለጎበኚዎች ምቹ ለማድረግ ገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት በመቅረጽ ወደ ተግባር የተገባ ስሆን የፕሮጀክቱ ግንባታ ሂደቱ እተጠናቀቄ ይገኛል፡፡ለሁለቱም ዞኖች ህዝብ ለልማት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በመፍታት የልማት ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ከማስቻሉም ባለፈ የወደፊት ተስፋቸዉ እንድለመልምና በሀገርና በአለም ደረጃ የአከባቢውን በጎ ገጽታን በማጉላትና በማስተዋወቅ አይነተኛ ሚና ይጨወታል፡፡
ፕሮጀክቱ በአከባቢ ለሚገኙ ለበርካታ ወጣቶችና ሴቶች በስፋት የሥራ ዕድል የፈጠረ ስሆን በብሄራዊ ፓርክ ዙሪያ የሚገኙ ማህበረሰብ ክፍሎች በዘላቅነት ከቱሪዝም ዘርፍ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግና ከጨበራ እስከ ጩርጩራ ድረስ ያለውን የመንገድ መሰረተ ልማት በማስከፈት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጠናከር መደረጉ ትልቅ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ፋይዳዎች ይኖሩታል ብለን እናምናለን፡፡

የመረጃ ምንጭ፡- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የቱሪዝም መስህቦች ጥናት ጥበቃና ልማት ዳይረክቶሬት ነው