የደ/ም ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ መልዕክት

Amharic
bimage: 
bbody: 

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ከነባሩ ደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች ክልል መንግሰት ህዳር 14/2014 ዓ.ም በህዝበ ውሳኔ የተወለደ ክልል ሲሆን በውስጡም ስድስት ዞኖችን ማለትም ካፋ፣ዳውሮ፣ ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ምዕራብ ኦሞ እና ኮንታ ይገኙበታል። አለም ወደ አንድ መንደር በመጣችበት በዚህ ጊዜ ሀገራችን ኢትዮጵያ ካደጉት ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ ‘ኢትዮጵያ ዲጂታላይዘሽን 2025’በሚል ብዙ ተግባራትን በቴክኖሎጂ ዘርፍ በማከናወን ላይ ትገኛለች፡፡ ክልላችን በውስጡ የያዛቸውን የተፈጥሮ ሀብት፣ባህልና ቅርስ አስተሳስሮ ለዓለም ህብረተሰብ ለማስተዋወቅ ብሎም የዲሞክራሲ፣የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን በቴክኖሎጂ አስደግፎ ተደራሽ ለማድረግ እና የግብርና ውጤቶችና የተለያዩ ማዕድናትን( ወርቅ፣የድንጋያ ከሰል) ፣ ሰፊ የኢንቨስትሜንት መሬት፣ የውሃ ሀብቶችን እንዲጎበኝ የድህረ- ገጽ ልማት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡
በመሆኑም ክልላችን ይህንን ድህረ-ገጽ በማልማት የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን፣ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን፣ የመንግስት የዲሞክራሲ፣የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለተገልጋዩ ህብረተሰብና ለዓለም ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ በየደረጃው ካለው ባለቤትና ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ጥረቶች ተደርጓል። ስለሆነም የክልላችንን ድህረ-ገጽ በማየት መረጃ በማግኘት የተለያዩ የቱርዝም መዳረሻ ቦታዎችን መጎብኘት፣ ኢንቨስት ለማድረግ ከፈለጉ ከክልሉ መንግስት ጋር አብሮ መስራት የሚቻል ስለሆነ ከሀገር ውስጥም ሆነ ውጪ ያላቹ ሀገርዎንና ራስዎን ተጠቃሚ እንዲያደረጉ ጥሪ እናቀርባለን።